የመውሊድ በዓል በሀረር እና ጎንደር ከተሞች ተከበረ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 497ኛው የመውሊድ በዓል በሀረር እና ጎንደር ከተሞች
ተከብሯል፡፡
በዓሉ በሐረር ከተማ እየተከበረ ሲሆን በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነብዩ መሐመድን ልደት
አክብረዋል፡፡
ምዕመናኑ ነብዩ በህይወት በነበሩበት ወቅት ይፈፅሟቸው የነበሩ መልካም ነገሮችን በማንሳትና በማወደስ ነብዩን አስበዋል።
በበዓሉ ህዝብ መስሊሙ እርስ በእርስ መዋደድና መደጋገፍን እሴቱ ሊያደርገው እንደሚገባ በበዓሉ ላይ የተገኙ ምዕመናን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የመውሊድ በዓል በጎንደር ከተማ ጃሚ አልከቢር መስጅድ ተከብሯል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሀይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።
በተሾመ ኃይሉ እና ኤልያስ አንሙት