Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዓሉን ሲያከብር በተለያየ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳት እና በመደገፍ ማክበር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በዓሉ የሚከበረው ሀገራችን የገጠማትን ፈተና በጠንካራና በተባበረ ክንዳችን በመመከት የሀገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ መንግስት በትኩረት እየሰራ በሚገኝበት ሠዓት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በዓሉ  የሰላም ፣የፍቅር፣የመቻቻል፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.