በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጀ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭት ለተጎዱ ወገኖች “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” በሚል መርሕ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።
መድረኩ በካናዳ እና አሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች በበይነ-መረብ አማካኝነት እንደሚካሄድ ታውቋል።
በመድረኩ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በሁለቱ ሀገራት የኢፌዴሪ አምባሳደሮች እንዲሁም የአደረጃጀቶች አመራሮች እና አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመድረኩ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ 400 ሺህ ዶላር ይሰባሰብበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!