Fana: At a Speed of Life!

የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በአምቦ ከተማ ተከብሯል፡፡
 
በአከባበር ስነ ስርዓቱ የቱለማ አባ ገዳ እና የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ጉባኤ ሰብሳቢ አባ ገዳ ጎበና ሆላን ጨምሮ የመጫ አባ ገዳ እና የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ጉባኤ ጸሐፊ አባ ገዳ ወርቅና ተሬሳ እንዲሁም ሃደ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል፡፡
 
የበዓሉ ተሳታፊዎች÷ የኢሬቻ ሆረ አምቦ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም መከበር መጀመሩ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.