የሀገር ውስጥ ዜና

ለ12ኛ ክፍል ፈታኞች እና አስተባባሪዎች ስለ ፈተናው አሰጣጥ ገለጻ ተደረገ

By Melaku Gedif

October 08, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ፈታኞች እና አስተባባሪዎች ስለ ፈተናው አሰጣጥ በየ ዩኒቨርሲዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና የፊታችን መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ይሳጣል፡፡

ለዚህም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ወደ ሚወስዱበት ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለትም ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ፈታኞች እና አስተባባሪዎች በፈተናው አሰጣጥ ዙሪያ በየ ዩኒቨርሲዎች ገለጻ ሲደርግ መዋሉ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!