ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ።
ሙዚየሙን የጎበኙት ጋዜጠኞች ከጋና፣ ካሜሮን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኒጀርና ሌሎች አገሮች የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በጉብኝታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውን በመግለፅ÷ ኢትዮጵያ ለሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ይህ የኢትዮጵያ መልካም ተሞክሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲስፋፋ በዘገባዎቻቸው እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በመሃል አዲስ አበባ በአስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ማራኪ ጉልላት ይዞ የተገነባው የሳይንስ ሙዚየም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል።
ሙዚየሙ ሳይንስና ጥበብን በጋራ አጣምሮ በያዘ የኪነ-ህንጻ ንድፍ የተገነባ ሲሆን÷ኪነህንጻው የያዘው ክብ ቅርፅም በማያቋርጥ ሂደት ውስጥ ያለ እድገትንና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።
በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!