Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ሁለት የሴካፋ ውድድር ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ከመስከረም 23 ቀን 2015 ጀምሮ በአበበ በቂላ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም ዛሬ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች የሚከናወኑ ሲሆን፥ በምድብ አንድ ከቀኑ 7 ሰዓት ለግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ሶማሊያና ታንዛንያ ይጫወታሉ።

በምድብ ሁለት ከቀኑ 10 ሰዓት ቡሩንዲ ከደቡብ ሱዳን ይጫወታሉ።

ጨዋታውን የሚያሸንፈው ብሔራዊ ቡድን በዚሁ ምድብ በስድስት ነጥብ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያለፈችውን ኡጋንዳን ይቀላቀላል።

በምድብ አንድ ተደልድላ የነበረችው ኢትዮጵያ በምድቡ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች ተሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር መሸጋገር አልቻለችም።

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቆይ ታውቋል፡፡

በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ አገራት በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ዞኑን ወክለው እንደሚሳተፉ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.