Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በፋፈን የሚገኘው ዘመናዊ የግመል ማራቢያ ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን የሚገኘው ዘመናዊ የግመል ማራቢያ ማዕከልን ጎበኙ፡፡

የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከትናንት በስቲያ ጅግጅጋ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባውን በጅግጅጋ አካሂዶ የተለያዩ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡

የኮሚቴው አባላት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን የሚገኘውን ዘመናዊ የግመል ማራቢያ ማዕከል መጎብኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ የኮሚቴው አባላት በዞኑ ሸቤለይ የሚለማው ዘመናዊ የፍራፍሬ እርሻዎችን ጎብኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.