Fana: At a Speed of Life!

ሶማሌ ክልል ድርቅን በራስ የስንዴ ምርት መከላከል የሚያስችል አቅም ፈጥሯል – ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የሚከሰተውን ድርቅን በእርዳታ ሳይሆን በራስ የስንዴ ምርት መከላከል የሚያስችል አቅም መፈጠሩን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በክልሉ ፋፋን ዞን ቱሉ ጉሌት ወረዳ በተካሄደው የ2015 የበጋ መስኖ ስንዴ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ነው፡፡

ድርቅን ሁል ጊዜ በእርዳታ መከላከል አይቻልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በተደጋጋሚ ከህዝባችን የሚቀርበው ጥያቄ በክልሉ የሚፈጠረውን ድርቅ ለመከላከል በዘላቂነት ምን እየሰራችሁ ነው የሚል ነበር ብለዋል፡፡

ሆኖም አሁን ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የእርዳታ እህል እንዴት መቀጠል ይቻላል የሚለው የሕዝባችን የዘወትር ጥያቄ ምላሽ እያገኘ መሆኑንም ነው ያነሱት።

ልዩ ትኩረት በመስጠት የለማው ከ847 ሺህ በላይ ሔክታር የስንዴ ምርት በክልሉ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ችግር ለመቅረፍ ነውም ብለዋል፡፡

በክልሉ ሊለማ ከሚችለው መሬት 10 በመቶ ማልማት መቻሉን ጠቁመውም ፥ ከአሁን በፊት ከ5 በመቶ በታች የነበረውን የምርት አቅም ወደ 10 በመቶ ማሳደግ የተቻለበት ዓመት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ምርቱን ለማሳደግ አሁንም ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በዓመቱ ስንዴን ኤክስፖርት የማድረግ ውጥን እንዲሳካ ሶማሌ ክልል 2 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የበጋ መስኖ ስንዴን የማጠናከር ሥራ በሰፊው እንደሚሰራም ነው ያስታወቁት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.