Fana: At a Speed of Life!

ከ560 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን እየወሰዱ ነው- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ560 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በ130 ማእከላት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው በሐዋሳ ዋናው ግቢ በድልድይ መደርመስ ምክንያት በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱን እና የተጎዱ ተማሪዎች ህክምና እያገኙ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኝ የሆኑ ከአንድ ወረዳ የሶስት ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ፈተናውን መፈተን እንደማይፈልጉ ገልፀው ለቀው መውጣታቸው የተገለፀ ሲሆን÷ “ምክንያቱ በአግባቡ ተጣርቶ እርምጃ ይወሰዳል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ውጪ ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ግቢ እና ስድስት ኪሎ በዋናው ግቢ የሚሰጠው ፈተና ተጎብኝቷል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.