Fana: At a Speed of Life!

ለጎረቤት ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ሃይል ከ13 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ሁለት ወራት ለሱዳንና ጂቡቲ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ከ13 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ሽያጭ መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
 
በተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት መምሪያ የሽያጭና ደንበኞች አስተዳደር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ ምኒሊክ ጌታሁን÷ ባለፉት ሁለት ወራት ለሱዳን እና ጂቡቲ ከ349 ነጥብ 56 ሚሊየን ኪሎ ዋት ዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ በሁለቱ ወራት 232 ነጥብ 76 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የ13 ነጥብ 04 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሽያጭ በማከናወን የዕቅዱን 70 ነጥብ 29 በመቶ ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡
 
ለሱዳን 112 ነጥብ 36 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት ኃይል በማቅረብ የ5 ነጥብ 61 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን ÷ ለጂቡቲ ደግሞ 120 ነጥብ 39 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የ7 ነጥብ 42 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡
 
ለጅቡቲ ለማቅረብ በዕቅድ ከተያዘው ኃይል የ12 ነጥብ 29 በመቶ ብልጫ ያለው ኃይል መቅረቡን ገልጸው ÷ ለሱዳን የዕቅዱን 46 ነጥብ 36 በመቶ ብቻ መሸጥ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በሁለቱ ወራት ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ከተገኘው ገቢ በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ2 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር በላይ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.