Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የሀገርን ጥቅም ባስከበረ መልኩ ለሰላም ውይይት ጥረት ማድረጉን ይገፋበታል-ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የሀገርን ጥቅም ባስከበረ መልኩና ዘለቄታን ባማከለ መልኩ የሰላም ውይይት እንዲደረግ የተቻለውን ጥረት ማድረጉን እንደሚገፋበት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የ2015 በጀት ዓመት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር በ2014 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶችን በማረም እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የሰላምንና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች አንገብጋቢ መሆናቸውን በመረዳት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መንግስት ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የሀገርን ጥቅም እና ዘለቄታን ባማከለ መልኩ የሰላም ውይይት እንዲደረግ የተቻለውን ጥረት ማድረጉን እንደሚገፋበት ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል፡፡

ነገር ግን ይህንን የሰላም አማራጭ በመርገጥ ለሚደረግ ማንኛውም ትንኮሳ አስፈላጊው እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራውን በተሳለጠ መልኩ ይሰራ ዘንድ ለሚመጡት ሀሳቦችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት መንግስት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት የሀገራችን ዘላቂ ጥቅም በሚያስጠበቅ መልኩ ከውጭ ወዳጅ ሀገራት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አማራጭ መሆኗን የሚያስተዋውቁ የተለያዩ የማስተዋወቅ ስራዎችን በመስራት አቅም ያላቸውን ባለሃብቶች ለመሳብ በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ይሰራል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ ከግድቡ ጋር የሚነሱ ማንኛውንም አይነት ጥያቄዎች ከኢትዮጵያ ተጠቃሚነት አንፃር በመመርመር አስፈላጊውን ውይይትና ድርድር ማድረጋችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በፍትህ እጦት ወይም መዘግየት በከፍተኛ ደረጃ የህዝብ እሮሮ መኖሩን በመገንዘብ ህዝቡን ያሳተፉ ማሻሻያዎች በማድረግ ቀልጣፋ እና ግልጽ አሰራር በመዘርጋት የተገልጋዩን የፍትህ ጥማት ለማርካት በቅንጅት እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡

በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ጥልቅና ተግባር ተኮር ስራ እንደሚሰራና የችግሩ ምንጭ የሆኑ አሰራሮችንና ሰራተኞችን በመለየት ተገቢው ማስተካከያ እንደሚወሰድም ነው የተናገሩት፡፡

በማህበራዊ ዘርፍ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ስራዎችን በማጠናቀቅ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው፡፡

ከጦርነት ጋር ተያይዞ የወደሙ ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ማስገባት ቀጣይ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

መንግስት የታክስ ገቢን ማሻሻል፣ የሀብት ብክንነትን መቀነስ፣ የመንግስት በጀትን ለድህነት ቅነሳ ማዋል፣ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና ጤናማ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲኖር ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርግም አውስተዋል።

በበጀት ዓመቱ ግጭቶችን በውይይት በመፍታትና የምክክር ኮሚሽኑን ወደፊት በማራመድ ልማትን በተጀመረው መንገድ በማስቀጠል፥ ህዝቡ ካጋጠመው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማላቀቅ በከፍተኛ ደረጃ የምንነሳሳበት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ፡፡

በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ጥልቅና ተግባር ተኮር ስራ እንደሚሰራና የችግሩ ምንጭ የሆኑ አሰራሮችንና ሰራተኞችን በመለየት ተገቢው ማስተካከያ እንደሚወሰድም ነው የተናገሩት፡፡

በማህበራዊ ዘርፍ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ስራዎችን በማጠናቀቅ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡

ከጦርነት ጋር ተያይዞ የወደሙ ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ማስገባት ቀጣይ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

መንግስት የታክስ ገቢን ማሻሻል፣ የሀብት ብክንነትን መቀነስ፣ የመንግስት በጀትን ለድህነት ቅነሳ ማዋል፣ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና ጤናማ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲኖር ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

በበጀት ዓመቱ ግጭቶችን በውይይት በመፍታትና የምክክር ኮሚሽኑን ወደፊት በማራመድ ልማቱን በተጀመረው መንገድ እናስቀጥላለንም ነው ያሉት።

አያይዘውም ህዝቡ ካጋጠመው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማላቀቅ በከፍተኛ ደረጃ የምንነሳሳበት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ፡፡
በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.