ስፓርት

ኬንያዊው አትሌት ፊሌሞን ካቼራን አበረታች ንጥረ-ነገር በመጠቀሙ ለሦስት ዓመታት ከውድድር ታገደ

By Alemayehu Geremew

October 10, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኬንያዊው አትሌት ፊሌሞን ካቼራን አበረታች ንጥረ-ነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ ለሦስት ዓመታት ከውድድር ታገደ፡፡

የአበረታች ንጥረ-ነገር ምርመራ ሳይደረግለት እና በ”አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት” ሳይታገድ በፊት አትሌቱ በጋራ ብልፅግና ሀገራት (ኮመንዌልዝ) ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ የኬንያን የማራቶን ቡድን አባላት ተቀላቅሎ ነበር፡፡

ከአትሌት ፊሌሞን ካቼራን ዕገዳ በኋላም ቀደም ሲል ለኬንያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቶ የነበረው አትሌት ሚካዔል ጊታኤ መተካቱን ሲጂቲ ኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡

በመሆኑም አትሌት ሚካዔል ጊታኤ ከኤሪክ ኪፕታኑ እና ጆናታን ኮሪር ጋር በመሆን ኬንያን ወክለው በማራቶን ውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡