የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት በጂቡቲ ጦር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ

By ዮሐንስ ደርበው

October 10, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት በጂቡቲ መከላከያ ሰራዊት ታጁራህ ክፍለ ጦር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፥ ለተጎጂ ቤተሰቦች ለጂቡቲ ህዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።