Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ሦስተኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሦስተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ አስጀመሩ፡፡

የሳይበር ደህንነት ወርን በማስመልከት የተዘጋጀውን ዓውደ ርዕይም መርቀውው ከፍተዋል፡፡

“የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ለሀገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር መክፈቻ ፕሮግራም በስካይላይት ሆቴል ተካሄዷል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ለመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ፥ ሚኒስትሮች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.