Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ ለሚመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሚና የላቀ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደገ ሀገር በጤናው ዘርፍ ለሚመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሚና የላቀ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት አሠራሩን በማዘመን የአቅርቦት ሰንሰለቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ከያዛቸው እቅዶች አንዱ ERP (Entreprise Resource Planning) መተግበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በማቋቋም ሲዶር ከተባለ ዓለም ዓቀፍ የሶፍትዌር አቅራቢ ድርጅት ጋር የፊርማ ስነስርዓት አከናውነዋል፡፡

ዶክተር ሊያ ታደሰ በስምምነቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀው÷ ይህንን ስኬት እውን ለማድረግም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሚና የላቀ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት÷ ተቋሙ በአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ SMILE ፕሮጀክት መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ በጀትም በአጠቃላይ 9 ሚሊየን ዶላር ወይም 476 ሚሊየን ብር መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.