Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት ከ80 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለመከላከያ ሰራዊት ከ80 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የግብርና ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ 9 ተጠሪ ተቋማት ናቸው።

ድጋፉን ያስረከቡት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የሚኒስትሩ ተወካይ እያሱ ኤልያስ፥ ሚኒስቴሩ ከ80 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ፣ የቀንድ ከብት እና ሌሎች ምግብ ነክ ድጋፎች ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ÷ ለድጋፉ ምስጋና አቅርበው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

 

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.