Fana: At a Speed of Life!

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ አልፈው በአፍሪካ ገበያ ውጤታማ መሆን ይችላሉ – ገርድ ሙለር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ አልፈው በአፍሪካም ገበያ ውጤታማ መሆን ይችላሉ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ገርድ ሙለር ተናገሩ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ገርድ ሙለር ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ መላኩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ለተቀናጀ አግሮ ኢንዲስትሪ ፓርኮች ልማት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በቆዳና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው፡፡

ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የተደረገው የቴክኒክ ድጋፍ አበረታች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማት ማደግ የሚያግዙ የምግብ ማቀነባበር፣ ጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ልማትን የሚያፋጥኑ ድጋፎች መደረጋቸው ኢትዮጵያ የያዘችውን የኢንዱስትሪ ልማት ግቦች እንድታሳካ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ገርድ ሙለር በበኩላቸው÷ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ በተሰማሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገቡ ባለሀብቶችን ለመሳብ ጠንካራና ተከታታይነት ያላቸው የማስታወቂያና ሌሎች ሁነቶችን በጋራ በመሥራት ዘርፉን ለማሳደግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ሲያፈሱ ሰፊ የገበያ ዕድል እና የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልጸው÷ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ገበያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ገበያም ውጤታማ መሆን እንደሚችሉም ነው የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.