Fana: At a Speed of Life!

በሰሜንና የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ፀሐያማና ነፋሻማ የዓየር ሁኔታው ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ይቆያል – ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜንና የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የተስተዋለው ፀሐያማና ነፋሻማ የዓየር ሁኔታ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት የሚቆይ መሆኑን የብሄራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረውን የዓየር ሁኔታ በተመለከተ የትንበያ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኛው የሰሜንና የሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖ ሊቆይ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

አልፎ አልፎ በሚጠናከሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ምክንያት በአንዳንድ የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከአነስተኛ እሰከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚያገኙ  ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው፡፡

በተጨማሪም የደቡብና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀን ወደ ቀን ከሚሻሻለዉ እርጥበታማዉ የዓየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በዚህም መሰረት በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚያገኙም ነው የሚጠበቀው፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ ምስራቃዊ ክፍል ደግሞ በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ አነስተኛ ዝናብ የሚኖር ሲሆን ፥ የተቀሩት አካባቢዎችዎች ደረቅ ሆነው እንደሚቆዩ ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.