Fana: At a Speed of Life!

አቶ ቀጄላ መርዳሳ ከዩኔስኮ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ከዩኔስኮ የኢትዮጵያ ዳይሬክተርና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የዩኔስኮ ተወካይ ዶ/ር ሪታ ቢሶናውት ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (የዩኔስኮ) የ2005 ኮንቬንሽን አተገባበር ክትትልን በሚመለከት፣ የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲን ለመተግበር በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርጅቱ ስለሚሰጠው ድጋፍ፣ በዕይታዊ ጥበባት ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሰዓልያን ድጋፍ ስለሚያገኙበት ሁኔታን ዳሰዋል፡፡

በተጨማሪም የባህል መረጃዎች አሰባሰብ ሥርዓት ስለሚዘረጋበት ጉዳይ፣ በአዲሱ ሳይንስ ሙዚዬም የኢትዮጵያ ባህል፣ የጥበብ ውጤቶችና ቅርሶች ስለሚተዋወቁበት ሁኔታ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት የጎንዮሽ ትስስር ስለሚፈጥሩበት ሁኔታም ነው የመከሩት፡፡

በቀጣይም የሁለቱን ተቋማት ተልዕኮዎች ለማስፈጸም የሚያግዙና በጋራ የሚሠሩ ቁልፍ ተግባራት በጋራ ተለይተው የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ እንደሆነ መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.