አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ የያዙ አስር የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ የያዙ አስር የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው።
የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ የያዘ ቡድን በኤክስፖው እየተሳተፈ ነው።
ቡድኑ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚቆየው የዱባይ ቴክኖሎጂና አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ ለመሳተፍ ነው ያቀናው።
በኤክክፖው ከ170 በላይ ሀገራት የመጡ ታላላቅ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ፡፡
በኤክስፖው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ አስር አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን በማሳተፍ ምርትና አገልጎሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እያደረገች ነው፡፡
በዚህም በተለየዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉና ባለሃብቶች ጋር እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል መባሉን የኢንቬሽንና ቴክኖሊጅ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!