Fana: At a Speed of Life!

አቶ ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ አቶ አበበ ሃይለገብርኤል ጋር ተወያዩ ፡፡

በውይይታቸውም የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳች ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ድርጅቱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለውን የምግብ ቀውስ ለመቀነስ አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው ተመላክቷል፡፡

አቶ ዑመር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት በኢትዮጵያ እያበረከተ ለሚገኘው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.