Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የነዋሪዎች የዜግነት አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የነዋሪዎች የዜግነት አገልግሎት በይፋ መታወጁን የክልሉ ርዕሰ መስታደድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።

ቫይረሱ የዓለም ስጋት መሆኑ ከታወጀ መቆየቱን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደሀገር ብሎም በክልል ደረጃ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ወደ ተጨባጭ ስራ ተገብቷል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ዕለት ተዕለት ከሚያከናውኑት ስራ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተያዘውን አቅድ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ መሰረት በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮች ኮሚቴ አቋቁመው ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን መረጃ እየሰጡ ይገኛለ ነው ያሉት።

ከጤና ዘርፉ ጋር በመሆንም መከላከል እና ቁጥጥር ላይ ግንዛቤ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶም እየተሰራ እንደሚገኝ ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እስከአሁን ቫይረሱን ለመከላከል የጤና ባለሙያዎች ላከናወኑት ስራም ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.