የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሮና ቫይረስ አስጊ በመሆኑ ማንኛውም ሙስሊም በቤት ውስጥ መስገድ እንደሚችል ምክር ቤቱ ገለፀ

By Tibebu Kebede

March 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ማንኛውም ሙስሊም የኮሮና ቫይረስ አስጊ በመሆኑ ከጁምዓ እና ጀመዓ መቅረት በሸርዓ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል። በመሆኑንም ህዝበ ሙስሊሙ በየቤቱ መስገድ እደሚችል ነው ምክር ቤት የገለፀው።