የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከደቡበ ኮሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

October 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የደቡበ ኮሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ኪም ጂን-ፒዮን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢኮኖሚ ትብብርና የፓርላማ ግንኙነትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በፈረንጆቹ ከ1950 እስከ 53 በኮሪያ ጦርነት ወቅት ደቡብ ኮሪያን ለመደገፍ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን መላኳን አስታውሰዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በደም ዋጋ የከፈሉ የረጅም ጊዜ ወዳጆች ናቸውም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!