Fana: At a Speed of Life!

በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም -የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም ሲል የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገለጸ፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩን አስመልክቶ በስተላለፈው መልዕክት÷ በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሀገር አለኝታ የሆነ ትውልድ የማፍራት ርዕይን የሚጻረር ነው፡፡

ስለሆነም ድርጊቱ በሰው ልጅ ላይ ከሚፈጸም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተለይቶ የሚታይ አይደለም ነው ያለው፡፡

መንግሥት ለዚህ ጉዳይ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የምዘና ሥርዓቱ የትምህርት ጥራትን ብቻ ሳይሆን የተማረ ሰው ሃይልን ከፍታ በሚያስጠብቅ እና የምዘና ስርዓቱን ስብራቶች ለዘለቄታው በሚጠግን መንገድ የመጓዝ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑም አንስቷል።

በመንግሥት እየተወሰደ ያለውን የስርዓተ ትምህርት ለውጥም ሆነ የምዘና ሥርዓት ውጤታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ አሠራሮችን መደገፍና ለተፈፃሚነታቸው መተባበር ለመንግሥት እና ለትምህርት አመራርና ተቋማቱ ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በእውቀት የበለፀገ፣ አመለካከቱ ያደገ፣ በክህሎቱ የተካነ እና ውጤታማ የሆነ ትውልድ የመፍጠር ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ እንደሆነ ማስገንዘቡንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የምዘና ሥርዓቱ ያለበትን ትውልድ አጥፊ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.