Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ልጅ በሠላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ61 ሴንቲ ሜትር ርዝመት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ በኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ተብላ የተመዘገበችው ኤሻሌ ወርቁ ሴት ልጅ በሠላም ተገላግላለች።

ኤሻሌ ወርቁ በወላይታ ሶዶ ዞን በሚገኘው ክርስቲያን ሆስፒታል ጠዋት 3 ሠዓት ላይ መውለዷን የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዓለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ሥራ አስኪያጁ ድርጅቱ ኤሻሌ ወርቁን በ61 ሴንቲ ሜትር ርዝመት የኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ብሎ መመዝገቡን አስታውሰዋል፡፡

ኤሻሌ ወርቁ የሰባት ወራት የእርግዝና ጊዜ እንደነበራትና በሕክምና ክትትል በቀዶ ጥገና እንደወለደችም ነው ሥራ አስኪያጁ ጨምረው የጠቆሙት፡፡

የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዓለም ÷ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ዓለም ላይ 61 ሴንቲ ሜትር ቁመት ርዝመት ያላት እናት መውለዷን የሚጠቁም መረጃ እንደሌላቸው ጠቁመዋል።

ምናልባትም በዚህ የቁመት ልክ በመውለድ የዓለም አጭሯ ሴት ልትሆን እንደምትችል ያላቸውን ግምት ገልጸውልናል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.