Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ብረት አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ለማቅረብ መስማማታቸውን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ፡፡

አቅርቦቱ የሚከናወነው አሊጋስ፣ ኢዝሚርና እስክንድሪያ ከተሰኙ የቱርክ ወደቦች በመነሳት ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ከሚያቀርቡ ብረት አስመጪዎችና ወኪላቸው አርካስ ጋር በተደረሰ ስምምነት መሆኑንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ፥ አቅራቢዎች ቀልጣፋ አገልግሎትና በቅናሽ ዋጋ በጂቡቲ ወደብ መዳረሻዎች ለማጓጓዝ ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በቂ የብረት ምርት ማቅረብ እስከምትችል ድረስ በቱርክ ሀገር ብረት ከሚያቀርቡ አስመጪዎች የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ያማከለ አቅርቦት እንዲኖር በማጓጓዝ ረገድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ ወደቦች የራሷን መጫኛ መርከቦች በማሰማራት የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በመደበኛነት ወደ ቱርክ መጫኛ ወደቦች የራሱን መርከቦች እና ተጨማሪ ቻርተር መርከቦችን አሠማርቶ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.