Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም አቶ ደመቀ መኮንን የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት አንስተዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ በበኩላቸው፥ የሀገራቱ ግንኙነት ከተለመደው ወዳጅነት ባለፈ በጠንካራ አጋርነት ላይ የተመሰረ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሩዋንዳ አንድ የሆነች እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ማየት ትፈልጋለችም ብለዋል ሚኒስትሩ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.