Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብለው ከሚጠበቁ 595 ሺህ የማህበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ውስጥ 586 ሺህ 541 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ተብሏል።
ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።
ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱንም ነው የገለጸው።

 

የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ሳይለቁ  ቀጣይ ፈተናዎችን የወሰዱና ያለፍላጎታቸው አንድ ፈተና ያመለጣቸው ተፈታኞችም በሚቀጥለው ዙር ፈተናው እንደሚሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በፍላጎታቸው ጥለው የወጡ ተፈታኞችን ግን ዳግም የሚሰጠው ፈተና እንደማይመለከታቸው ተጠቁሟል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው አደጋ ፈተና ያልወሰዱትም በቀጣይ ይፈተናሉ ተብሏል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ለተፈጥሮ ሣይንስ የትምህርት መስክ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጥቅምት 8 ቀን ፣ 2015 መሰጠት እንደሚጀምር ታውቋል።

በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.