Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላኑን ወደ ጭነት አገልግሎት ቀየረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየርመንገድ አንድ የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላኑን ወደ ጭነት አገልግሎት (ካርጎ) የመቀየር ሥራውን አጠናቆ ይፋ አደረገ፡፡

የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላኑ ወደ ጭነት አገልግሎት የተቀየረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእስራኤሉ ኤሮስፔስ ጋር በመተባበር ነው፡፡

የመቀየር ሥራውም ወደ ስድስት ወራት ገደማ ወስዷል፡፡

የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላኑን ወደ ጭነት አገልግሎት ለመቀየር 14 ሚሊየን ዶላር ገደማ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ይህም በውጭ ሀገራት ቢሠራ ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ ሊፈጅ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የቅየራ ሥራው በአራት ወራት የሚጠናቀቅ ተጨማሪ አንድ አውሮፕላን የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ይፋ ተደርጓል።

የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ እቃ ማጓጓዣ የመቀየር ሥራ በአፍሪካ የመጀመሪያ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ አገልግሎት ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡

አየር መንገዱ ለ17 ዓመታት የተገለገለበትን የመንገደኞች አውሮፕላን ነው ወደ ተሟላ የጭነት አገልግሎት ቀይሮ ሥራ ያስጀመረው፡፡

በአብርሃም ፈቀደ እና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.