የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ፍርድ ቤት በትብብር ለመሥራት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ፍርድ ቤት በትብብር ለመሥራት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የፈረሙት÷ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ እና የአፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኢማኒ ዳውድ ባውድ ናቸው፡፡
በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የልምድ ልውውጥን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር ይሠራሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ÷ስምምነቱ በተለይም በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ ለመሥራት ዕድል ይፈጥራል፡፡
ስምምነቱ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ጨምሮ የሥልጠና እና አውደ ጥናቶችን በጋራ ለማካሄድ የሚያስችል እንደሆነም አብራርተዋል።
ኢማኒ ዳውድ ባውድ በበኩላቸው ÷ ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ቁርጠኛ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ በሀገር ደረጃ ስምምነት ሲፈጽም ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመው ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!