Fana: At a Speed of Life!

የማኅበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እየሸኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማኅበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተቀበሏቸውን ተፈታኞች ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘት ጀምረዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የተቀበሏቸውን ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘት ጀምረዋል፡፡

እንዲሁም ወሎ፣ ወልቂጤ፣ አዳማ፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ድሬዳዋ፣ አርሲ፣ መቱ፣ ደምቢዶሎ፣ ወለጋ ፣ ጋምቤላ፣ ጂንካ፣ ወላይታ ሶዶ እና ዋቼሞ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹ ፈተናዎቻቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ የመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መሸኘት መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም 586 ሺህ 541 ተማሪዎች በማኅበራዊ ሣይንስ ዘርፍ ባለፉት ተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠውን ፈተና መውሰዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.