የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ የወጣቶች ልዑክ ጁባ ገባ

By Alemayehu Geremew

October 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ወንድማማችነት እና የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ ዓላማ ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ የወጣቶች ልዑክ ጁባ ገባ፡፡

ልዑኩ ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ÷ በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ እና የደቡብ ሱዳን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ ማሪዬ ቪልቩር አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአፍሪካ አህጉር ትስስር እና ትብብር እንዲጠናከር የተዘጋጁ ሁነቶች አካል ነው፡፡

የመጀመሪያውን ጉዞ ወደ ደቡብ ሱዳን በማቅናት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር እንደሚያከናውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-