Fana: At a Speed of Life!

አቶ አህመድ ሺዴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ቡድን አንድ ዋና ዳይሬክተር እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የዓለም ባንክ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ቡድን አንድ ዋና ዳይሬክተር ኢታ ማናቶኮ፣ ከአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አበበ አዕምሮሥላሴ እና ከምክትል ዳይሬክተሯ አና ሊሣ ፌዴሊኖ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሚሠሩ የልዑካን ቡድን መሪ እና የዴስክ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በድርጅቱ መካከል ያለው ግንኙነት በሚጠናከርበት በተለይም በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ መሠረት የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ ሽግሽግ ለማካሄድ ከአበዳሪ ሀገራት ጋር እየተደረገ ያለውን ውይይት በማፋጠን ተጨባጭ ውጤት እንዲኖረው በቀጣይ መከናወን ባለባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ልዑኩ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የፊስካል ጉዳዮች ዲፓርትመንት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የኢትዮጵያን የገቢ እና የታክስ አስተዳደር፣ ፐብሊክ ፋይናንስን ማጠናከር ስለሚቻልበት ሁኔታና ይህንንም ለማሳካት በጋራ ስለሚሰሩ የቴክኒክ ድጋፎች እና ትብብሮች ላይ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ መደረሱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.