Fana: At a Speed of Life!

ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ የአካባቢያቸው እየተመለሱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ የአካባቢያቸው እየተመለሱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ፈተናቸውን ከወሰዱባቸው የዩኒቨርሲቲ ማዕከላት ነው ወደ የአካባቢያቸው እየተመለሱ ያሉት።

ዩኒቨርሲቲዎችም መልካም ጉዞ በመመኘት ተማሪዎችን እየሸኙ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት መሰጠቱ ይታወቃል።

በሁለተኛው ዙር ፈተና የሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ የተመደቡበት የመፈተኛ ማዕከላት እንደሚገቡም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.