በዱባይና ሰሜን ኢሚሬቶች ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ከ303 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዱባይና ሰሜን ኢሚሬቶች የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት መንግስት ያቀረበውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ከ303 ሺህ ዶላር በላይ ተሰብስቧል።
ከድጋፉ ውስጥ 300 ሺህ የሚሆነው ከዱባይና ሰሜን ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማኅበር የተዋጣ ሲሆን፥ ዲፕሎማቶችና ግለሰቦችም ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
መንግስት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በልዩ ልዩ ሀገራት የሚገኙ የኢፌዴሪ ሚሲዮኖች የሀብት ማሰባሰብ ስራዎችን አጠናክረው ቀጥለዋል ነው የተባለው።
ከዚህ በፊት በአቡዳቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከዳያስፖራው ከ560 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።