Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የጣና ፎረም የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይካሄዳል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 10ኛው የጣና ፎረም የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚካሄድ አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፎረሙ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የፀጥታ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እንደሚካሄድና ለዚህም ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በፎረሙ ላይ የተቋማትና የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ 300 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ወደ ውቢቷ ባህር ዳር እየገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም ፎረሙ ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድም ነው የተናገሩት።

የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ የዜጎች ሚና ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይመክራል ብለዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመተባበር የተጀመረው የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ከዛሬ ጀምሮ በስድስት ሀገራት እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።

ለዚህም ጥቅምት 1 ቀን በተከላው ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች ሽኝት እንደተደረገላቸው ነው የገለጹት።

በደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ጂቡቲ ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራን የማኖር ስራም በሀገራቱ በኩል የተሟላ ድጋፍ እንደተሰጠው አንስተዋል።

ይህም የሀገራቱን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር የሚረዳና ኢትዮጵያ መሪ የሆነችባቸው የአህጉሪቱ የትብብር ስራዎችን ከፍ ወዳለ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ እንደሚታሰብም አስረድተዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.