Fana: At a Speed of Life!

ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ክሩዝ ሚሳዔል ሙከራ በማድረግ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያን አስጠነቀቀች፡፡

ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር አቅሟን ለማሳየት የረዥም ርቀት ክሩዝ ሚሳኤሎችን ሙከራ አድርጌያለሁ ብላለች፡፡

የሀገሪቷ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን በባህር ላይ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘጉ ሚሳኤሎች በተወነጨፈበት ወቅት በቦታው የተገኙ ሲሆን ፥ “ትልቅ እርካታ” እንደተሰማቸው መግለጻቸውን የሰሜን ኮሪያ የዜና አውታር (ኬ ሲ ኤን ኤ) ዘግቧል።

በዚህ የሚሳዔል ሙከራ “ጠላቶቼ ግልጽ ማስጠንቀቂያ እየሰጠኋችሁ መሆኑን እወቁት” ብለዋል ኪም፡፡

በቅርቡ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ ያደረገችው የረዥም ርቀት የክሩዝ ሚሳዔል ሙከራ ለዚህ ምላሽ እንደሆነ ነው ቲ አር ቲ በዘገባው ያመላከተው፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ አክለውም ፥ ሀገራቸው ማንኛውንም ወሳኝ ወታደራዊ ችግርና ጦርነትን በማንኛውም ጊዜ በቆራጥነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የኒውክሌር ሃይሏን ማጠናከር አለባትም ነው ያሉት።

ፒዮንግያንግ ካለፈው የፈረንጆቹ መስከረም 25 ቀን ጀምሮ ሰባተኛ የሆነውን የባለስቲክ ሚሳኤል ባለፈው እሑድ ማስወንጨፏ የሚታወስ ነው።

የሀገሪቱ ገዥ ፓርቲም የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እስከቀጠለ ድረስ የሚደረገው የሚሳኤል ሙከራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.