Fana: At a Speed of Life!

የመሰረተ ልማት ቅንጅትና መንገድ ዘርፍ እቅድ አፈጻጸም ሀገር አቀፍ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የመሰረተ ልማት ቅንጅትና መንገድ ዘርፍ እቅድ አፈጻጸም ሀገር አቀፍ ጉባዔ እያካሄደ ነው፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ÷ ጉባኤው በመሰረተ ልማት ቅንጅት ዘርፍ ተለይተው የተሰጡ ስራዎችን ከፌዴራል፣ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር ቅንጅት በመፍጠር በተሻለ ሁኔታ ለመተግበር  ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም  ጉባኤው በተገኙ ውጤቶችና ጉድለቶች ላይ ተወያይቶ የጋራ አቋም በመያዝ ወደተግባር ለመሸጋገር የተዘጋጀ መሆኑን  ነው የጠቆሙት ፡፡

በመድረኩ የዘርፉ የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷የ2015 በጀት ዓመት መነሻ እቅድ የጋራ ግቦች ላይም ውይይት ተደርጎ ትኩረት በሚሰጣቸው  ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.