በሀብሩ ወረዳ ለሚገኙ ከ14 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ለሚገኙ ከ14 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
በዚህ መሰረትም በሀብሩ ወረዳ ውስጥ በሊብሶ፣ መሃል አምባ እና ውርጌሳ ማዕከላት ተጠልለው ለሚገኙ 14 ሺህ 742 ተፈናቃዮች ድጋፍ መደረጉን ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በአካባቢው የነበረው ግጭት የህዝቡን የአኗኗር ሁኔታ በማወኩ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብና ለማሟላት አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበርም ተገልጿል።