Fana: At a Speed of Life!

ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው- ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ ለመከላከል እና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ሲሉ የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ፡፡

ዓለም አቀፍ የልጃገረዶች ቀን በደብረ ብርሀን ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

ሚኒስትሯ በበዓሉ አከባበር ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ጥቃቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ሁሉም አካላት የየድርሻቸውን አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ ይገባል፡፡

በተለይ ባለው የጸጥታ ችግር በሴቶች ላይ ውስብስብ የሆነ ማህበራዊ ችግሮች በመፈጠራቸው ሴቶች የበርካታ ችግሮች ገፈት ቀማሽ ሆነዋል ነው ያሉት።

ይህን በመረዳትም የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ በመከላከል እና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በእታገኝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.