Fana: At a Speed of Life!

የእድሜ እኩሌታ ቀውስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የእድሜ እኩሌታ ቀውስ እድሜ ካለፈ በኃላ እንደዚህ ባደርግ ኖሮ የሚል ፀፀትና ቁጭት መሆኑን የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

የዚህ ምክንቱ ደግሞ መስራት ባለብን ከምቾት ዞን ሳንወጣ የኖርንባቸው ዘመናት ውጤት ነው ይላሉ በጉዳዩ ላይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሃሳባቸውን የሰጡት የስነልቦና ባለሙያ ሲሳይ ተስፋዬ፡፡

እንደ ባለሙያው ገለፃ እስከ 30፣40 እና 50 ዓመት ሄደው ሰዎች ለራሳቸው ማዘጋጀት ያለባቸውን ነገሮች ሳያዘጋጁ ሲቀሩ ማለትም መማር ሲኖርባቸው ሳይማሩ ሲቀሩ ማግባት፣ መውለድ ሲገዳቸው ያን ሳያደርጉ ሲቀሩና የሚፈልጉትን ማግኘት አለመቻላቸውን ሲያዩ ይደነግጣሉ ይህም የህይወት ማዕበል ይባላል ነው የሚሉት፡፡

ከውስጥ ጥያቄ ይፈጠራል፤ ይህን መቋቋምም ከባድ እንደሚሆን ነው ያነሱት፡፡

ሰው በጊዜው የሚያስፈልገውን አላገኘም ማለት ደግሞ ጥሩ ያልሆኑ ሃሳቦች ይፈጠርበታል፤ ቤተሰብ አካባቢም አላገባህም/ሺም ፣አልወለድክም/ ሺም እራስህን አልቻልክም/ሺም፣ አልተማርክም/ሺም የሚሉ ጥያቂዎች ይመጣሉ እንዲሁም ከእኛ ቀድመው ያሉ ጓደኞቻችንን ስናይ የሚመጡ ሌሎች ጥቄዎችም ይኖራሉ ነው ያሉት፡፡

ይህ ደግሞ የስሜት፣ የፍላጎት እና ሌሎች ጉድለቶችን ይፈጥራል ያሉት የስነ ልቦና ባለሙያው በዚህ ቀውስ ውስጥ ደግሞ ከግለሰቡ አስተዋጽዖ በዘለለ ማህበረሰባዊ አገልግሎትም የራሳቸው ሚና እንዳላቸውም ይናገራሉ፡፡

በተለይም ግለሰቡ የህይወት ግቡን በትክክል እንዲረዳ እና ምክንታዊ ህይወት መምራት እንዲችል ንቃተ ህሊናውን በማዳበር ረገድ ስራ ከልተሰራ ግለሰቡ ዕድሜው አለአግባብ ሊባክን ይችላል ነው የሚሉት ባለሙያው፡፡

ዕድሜ ካለፈ በኋላ ለሚፈጠር ጥያቄ የተፈጠርንበት ዓላማ ማወቅ ወይም ወደእዚህ ዓለም የመጣንበትን ምክንያት ማወቅ መልስ ይሆናል ብለዋል አቶ ሲሳይ፡፡

ያለምክንያት ወደእዚህ ዓለም አልመጣንም፤ ድንቅ ፍጡርም ነን የሚሉት የስነ ልቦና ባለሙያው ለምን ምድር ላይ እኖራለሁ የሚለውን መመለስ እንደሚገባም ያነሳሉ።

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.