Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ግብዓቶችን ለገሱ

አዲስ አበባ፣መጋቢት13፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከያ`የህክምና ግብዓቶችን ለገሱ፡፡

ድጋፉንበአሜሪካን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ረስፖንስ ቲም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ግለሰቦችን በማስተባበር የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ በዓይነት በማሰባሰብ  የሰጡ ሲሆን÷ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትየሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝም ነው ተብሏል፡፡

ስርጭቱን ለመግታት የተላከው የህክምና ቁሳቁሥ ግብዓትም ለኢትዮጵያ ጤና ሚንስቴር  መላኩን  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር   ከአቶ ፍጹም አረጋ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.