በጋምቤላ ክልል ያለው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት በቂ ባለመሆኑ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ያለው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት በቂ ባለመሆኑ የተጀመረውን ለውጥ በዘላቂነት ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ፡፡
በጋምቤላ ክልል ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ንቅናቄና 11ኛው ክልል አቀፍ የጤና ዘርፍ ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ሽፋን ለማሻሻል ሰፊ ጥረቶች መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
አሁንም በክልሉ ያለው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት በቂ ባለመሆኑ የተጀመረውን ለውጥ በዘላቂነት ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ሮት ጋትዊች እንደገለጹት÷ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመደበኛ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ በጤናው ዘርፍ የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት አዳጋች ነበር፡፡
ከጤና ሚኒስቴር በመድረኩ ላይ የተገኙት ገሙ ቲሩ በበኩላቸው÷ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ መንግሥት በትኩረት እየሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!