Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን የመብረቅ አደጋ ሶስት የቤተሰብ አባላትን ህይወት አጠፋ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመብረቅ አደጋ እናትና አባትን ጨምሮ የሶስት ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ፡፡
 
የቀርሳ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው ÷ትናንት ሌሊት 9 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የመብረቅ አደጋ ሶስት የቤተሰብ አባላት ህይወት አልፏል።
 
በአደጋው የአራት አመት ህጻን ልጅን ጨምሮ ወላጅ እናትና አባትም ህይወታቸው ማለፉን በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ክትትል መርማሪ ኢንስፔክተር አህመድ ከማል ተናግረዋል።
 
አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእንደዚህ አይነት አደጋ ስለሚያጋልጥ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
 
በአብዱረህማን መሐመድ
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.