የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዜ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

October 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዜ አብዲ የተመራው የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ አዲስ አበባ ገቡ።

ለልዑኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ በሚካሄደው የጣና ፎረም ላይ ይካፈላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጣና ፎረም 10ኛ ዓመት ጉባዔ ከነገ ጥቅምት 4 እስከ 6/2015 በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!