Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በ10ኛው የጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ቆይታቸውም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢኮኖሚ፣ በአቅም ግንባታ እና በሌሎች ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማጠናከር ከመግባባት መድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ÷ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በባህል፣ ቋንቋ እና በታሪክ የተሳሰሩ አንድ ህዝቦች መሆናቸውን አውስተዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መልካም እድል እንደሚፈጥርም አንስተዋል፡፡

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በበኩላቸው ÷ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ትሰራለች ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.