Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ በጎረቤት ሀገራት ለማስፋፋት ያለመ ሁነት በጁባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ በጎረቤት ሀገራት ለማስፋፋት ታሳቢ ያደረገ ሁነት በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ተካሂዷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ሚኒስትር ዛዲግ አብረሃ፥ በዓለምአቀፍ ደረጃ ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ከደቡብ ሱዳን የነፃነት ትግል ጀምሮ የሀገሪቱ ሰላም እንዲረጋገጥ ኢትዮጵያ ያልተቋረጠ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷንም አስታውሰዋል ።

የደቡብ ሱዳን ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አልቢኞ አንቶኢዬ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ ተምሳሌት በመሆን በታሪክ ውስጥ ያበረከተችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሁልጊዜም በታሪክ ውስጥ እንደሚታወስ ነው የገለጹት፡፡

ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት በበርካታ ጉዳዮች በመስራት የሁለትዮሽ ግንኙነትቱ የላቀ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ÷በቀጣይ የሀገራቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሯ ይቀጥላል ብለዋል።

በዱቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ፥ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የአረንጓዴ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ በርካታ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህ በሀገር ውስጥ የተገኘውን ውጤት በጎረቤት ሀገራት በማስፋትና በመፈፀም ለቀጠናዊና ለአህጉራዊ ውህደት መነሻ እንደሚሆን ነው ያነሱት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.