Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ውይይት እንዲደረግባቸው የቀረቡለትን አጀንዳዎች አጽድቋል፡፡

በዚህም የአንድ የምክር ቤቱ አባል ያለመከሰስ መብት ማንሳትን ጨምሮ የምክር ቤቱ አንደኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለጉባዔን ተወያይቶ የሚያጸድቅ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.